ተዘውትረው የሚጠየቁ ጥያቄዎች።
ለጥያቄ መልስ ማግኘት ካልቻሉ፣ ምላሽ ለመስጠት እዚህ ያግኙን።
ዚንግ ምንድነው?
ዚንግ የአቻ-ለ-አቻ የመልዕክት መላኪያ፥ የስልክ ጥሪ ማድረጊያ እና የ ኢሜይል መተግበሪያ ነው። የተመሰጠሩ ኢሜሎችን እና ጽሑፎችን ሳይገለብጡ ወይም ሳያከማቹ መላክ የሚያስችል ቴክኖሎጂ በባለቤትነት መብት ያለው ነው። ዚንግ የመልዕክት ይዘትን ለማስተላለፍ ምንም አይነት ማከማቻ አይጠቀምም። ሁሉም ግንኙነቶች ግላዊ በሆነ መልኩ በ ላኪው እና በ ተቀባዩ መካከል ብቻ ናቸው።
ምንም አይነት ማከማቻ የሉም፥ የአቻ-ለ-አቻ ግላዊነት እንዴት ይሰራል?
ዚንግ ተጠቃሚዎችን በመሣሪያዎቻቸው መካከል ባለው የግል የበይነ መረብ መንገድ በመጠቀም እና በማገናኘት የራሳቸውን ውይይት እና ኢሜይሎች እንዲላላኩ ያስችላቸዋል። ዚንግ ለተጠናከረ ደህንነት መልዕክቶችን ወደ ትናንሽ መልዕክቶት በመቆራረጥ ለብቻው የሚልክ ሲሆን ምንም ዓይነት የመልዕክት ዱካ ለብቻው ተነባቢ አይሆንም።
ዚንግን ማን ሊጠቀም ይችላል?
ሁሉም ሰው! ነገር ግን እንዳየነው ከሆነ ተጠቃሚዎቻችን፡ ● ስለ ግንኙነታቸው ግላዊነት ስጋት የሚገባቸው ● ግላዊ እና ሚስጥራዊ የሆነ መረጃን በመደበኛው ድር ላይ ለመላክ ጭንቀት የሚገባቸው ● ኩባንያዎች ውሂባቸውን እየተከታተሉ እንደሆነ የሚያምኑ ● ሶስተኛ ወገኖች መረጃቸውን በተንኮል መልኩ ይጠቀምብናል ብለው የሚያስቡ።
መተግበሪያው ለመጠቀም ነፃ ነውን?
አዎ፣ የእኛ የ ተጠቃሚዎችን ስሪት ለመጠቀም ነፃ ነው ምክንያቱም ግላዊነት የዋጋ ተመን ስለሌለው።
ከሌሎች የመልእክት መላኪያ መተግበሪያዎች የሚለየው እንዴት ነው?
በብዛት ጥቅም ላይ ያሉ የጽሑፍ እና የመልእክት አገልግሎቶች ሰጪዎች የምትልኩትን መልዕክት ሁሉ ወደ ማከማቻ ቛታቸው ይገለብጣሉ። ዚንግን የተለየ የሚያደርገው የ ተጠቃሚዎችን መልዕክቶች፣ ውይይቶች እና ኢሜይሎችን ለማመቻቸት የመረጃ ማጠራቀሚያ አለመጠቀሙ ነው። መልዕክቶች በላኪው እና በተቀባዩ ስልኮች ላይ ብቻ መገኘቱ ነው።
ጠለፋ ወይም የ ውሂብ መረጃ ማፈትለኮች ነበሩ?
አይ፣ በዚንግ ምንም አይነት ክስተቶች አልነበሩም። ምክንያቱም ዚንግ ነገር እንዳያፈተልክ መልዕክቶችን አንይዝም፣ አንመለከትም፣ አይተላለፍም ወይም አይጸናም።
የዚንግ መተግበሪያ ን ለመጠቀም ከ በይነ መረብ ወይም ከ ዋይ-ፋይ ጋር መገናኘት አለብኝ?
አዎ፣ የዚንግን ኢሜይል መልዕክቶችን፣ ፅሁፎችን ወይም ጥሪዎችን ለመላክ ወይም ለመቀበል የ በይነ መረብ ግንኙነት ሊኖር ይገባል።
ስልኬ ከጠፋ/ ከ ተሰረቀ ምን ማድረግ አለብኝ?
የዚንግ መለያ ከሁለተኛ ስልክ ጋር ከተያያዘ ወደ ሁለተኛው ስልክዎ ገብተው የጠፋውን ወይም የተሰረቀውን ስልክ ማላቀቅ ይችላሉ። እንዲሁም የእርስዎን መረጃ ለመጠበቅ የሚስጥር መለያ ወይንም ፒን ማከል ይችላሉ። ዚንግ የትኛውንም የእርስዎን መልዕክቶች ወይም ውሂብ ስለማይዝ፣ የትኛውንም የእርስዎን መልዕክቶች ወይም ውሂብ ወደነበረበት መመለስ አንችልም።
ስልኬ ከጠፋ እና ከ መለያ ዬ ጋር የተገናኘ ሁለተኛ ስልክ ከሌለኝ ምን ማድረግ አለብኝ?
ዚንግ የትኛውንም የእርስዎን መልዕክቶች ወይም ውሂብ ስለማይዝ፣ የትኛውንም የእርስዎን መልዕክቶች ወይም ውሂብ ወደነበረበት መመለስ አንችልም።
ዚንግን በመጠቀም ልገኝ ወይም ልሰለል እችላለሁ?
ዚንግ ያሉበትን ቦታ አይከታተልም።
ዚንግን ለመጠቀም የትኛውን ዓይነት ስልክ/መሳሪያ መጠቀም እችላለው?
ዚንግ በሞባይል ስልክ (Android or IOS) ወይም ኮምፒዩተር መጠቀም ይችላሉ።
የዚንግ ተጠቃሚ ላልሆኑ ሰዎች መደወል ወይም መልዕክት መላክ እችላለው?
አይችሉም። መደወል ወይም መልዕክት መላክ የሚችሉት ለሌላ የዚንግ ተጠቃሚ ነው።
የዚንግ ተጠቃሚ ላልሆኑ ሰዎች ኢሜይል መላክ እችላለው?
አዎ ነገር ግን፣ ለ ዚንግ ተጠቃሚ ላልሆኑ የተላኩ ኢሜይሎች ግላዊ ወይም ደህንነታቸው የተጠበቀ ላይሆኑ ይችላሉ ምክንያቱም የተቀባዩ የኢሜል አቅራቢ የተቀበሏቸውን ኢሜይሎች በማዕከላዊ የዳታ ማጠራቀሚያ ላይ ሊያከማቹ ይችላሉ።